የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በሀላባ ዞን ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ሎት 1 አላቂ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች ሎት 2 የደንብ ልብስ ሎት3 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 4 ፈርኒቸር ሎት5 ሞተር ሳይክል የህትመት ሥራ(ባነር፣ ባጅ፣ መታወቂያ፣ የቢሮ ማህተሞች፣ የኃላፊ የስም ቲተር፣ ሰርተፊኬት) የሀላባ የባህል አልባሳት የወንድና የሴት እስታንዳርዱ የጠበቀ የቢሮ መጋረጃ የመብራት እቃዎች የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ጀነሬተሮች ስለዚህ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ (ታክስ ከሊራንስ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ21 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ:: ጨረታው በ22 ተኛ ቀን የጨረታው ሳጥን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ሆኖም ግን በመክፈቻው ቀን የተጫራቾች ያለመገኘት መምሪያው ጨረታውን ከመክፈት የሚያስተጓጉለው ነገር አይኖርም፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ ዋስትና በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 10% የውል ማስከበሪያ (CPO) ወይንም እንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው:: የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሀላባ ቁሊቶ source; modern tenders
